Tender Detail

Tender Details


በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ከሎት1-6 በተዘረዘረው መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአብክመ በሰ/ሽዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 01/2018

 

በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ከሎት1-6 በተዘረዘረው መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 - የፅህፈት መሳሪያ፤

ሎት 2 - ኮምፒውተር የምፒውተር መሳሪያዎች እና ተጓዳኝ እቃዎች፤

ሎት 3 - የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች፤

ሎት 4 - የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች፤

ሎት 5 - የቢሮ እቃዎች፤

ሎት 6 - ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፤

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  3. የማወዳደሪያ ዋጋው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ብቻ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ማ/ም/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሰራ ሰአት ማስገባት ይኖርባቸውል።
  8. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት ይቻላል በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥኑ ይታሸግ እና በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀናት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰአት መሰረት ጨረታው ይታሸጋል፤ ጨረታውም ይከፈታል።

  1. የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከመ/ማ/ም/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ።
  2. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወዲያውኑ ውል በመያዝ እቃውን በወረዳው በሚገኙ በየፑሉ ንብረት ክፍሎች ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
  3. ውድድሩ በጥቅል ድምር ወይም በነጠላ ሊሆን ይችላል።
  4. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-622-0516/ 0006 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

በአብክመ በሰ/ሽዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender