Tender Detail

Tender Details

  • Company Pawi Health Science College (የፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
  • Address ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912811777
  • Website
  • Deadline19 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityየእቃውን የጠቅላላ ዋጋ 1%
  • opening date2025-11-19 00:00:00
  • Categories Generators

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ለፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውል ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የመብራት ጀነሬተር በዘርፉ ከተሰማሩት አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Pawi Health Science College (የፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)


 

የጀነሬተር ግዥ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፓ/ጤ/ሳ/ኮ - 01/ 2018

 

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ለፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውል ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የመብራት ጀነሬተር በዘርፉ ከተሰማሩት አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያለው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No,) ማቅረብ የሚችል
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  4. የግዥውን መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1- 4 የተጠቀሰትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የሚገዛው ጀነሬተር አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Spesfication/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ገቢ በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000106922547 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖሲት ሲሊፕ ኦርጅናል ይዘው በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢን ቦንድ/ የእቃውን የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር አብረው በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማለትም ዋና እና ኮፒ በተለያዬ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር የመጀመሪያ ህንፃ ብሎክ “ሐ” የግዥ ስራ ክፍል 02 በመምጣት ለተከታታይ ቀናት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ 26/02/2018 ጀምሮ እስከ 10/03/2018 ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር የመጀመሪያ ህንፃ ብሎክ "ሐ" የግዥ ስራ ክፍል 02 በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 5፡30 ይከፈታል።
  11. የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  12. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0912811777/0920770257 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ።
  14. ተጫራቾች በሁሉም ዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያ ላይ ስርዝ ድልዝ እና በፍሉድ ከጠፋ ከውድድር ውጪ ይደርጋል፡፡

 

የፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

 

Save Tender