የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ባለ 110 ኪሎዋት ጀኔሬተር ግዥ በሰነድ ላይ ባለው መስፈርት መስረት በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የጀኔሬተር ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ባለ 110 ኪሎዋት ጀኔሬተር ግዥ በሰነድ ላይ ባለው መስፈርት መስረት በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚትችሉ መሆኑን እያሳወቅን።
- ተጫራቾች በዚህ የሥራ ዘርፍ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን፣ ቫት፣ የንግድ መዝገባ ሰነድ ማቅረብ አለባችው።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ.የተ አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአ/ግ/ህ/ሥ/ማ/ፌ የግዥ ክፍል በመገኘት ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11 ተከታታይ ቀናት ብቻ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀናት ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የዋጋውን 5% (አምስት በመቶ) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
- ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናልና ኮፒ እና የፋይናንሺያል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ12ኛዉ ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸዉ።
- ጨረታው በዚሁ እለት 4፡00 የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OAC ህንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12፤ ስልክ፡- 09-10-64-54-42::
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን
