Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ
  • Address ኮልፌ አጠና ተራ ከፖሊስ ጣቢያው ከፍ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-273-88-55
  • Website
  • Deadline19 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityለሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ በ1% የተሰላ ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር)
  • opening date2025-11-19 00:00:00
  • Categories Chemicals And Reagents , Medical Equipment And Supplies , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ የሚሆኑ የህክምና መገልገያ መሳሪያ፣ መድሀኒት እንዲሁም የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች ከህጋዊ አቅራቢዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የመለያ ቁጥር ኮ/ጤ/ጣ 03/824/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ የሚሆኑ

  1. የህክምና መገልገያ መሳሪያ፣ መድሀኒት እንዲሁም የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች ከህጋዊ አቅራቢዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  • የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  • የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፍኬት ያላቸው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  1. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ በ1% የተሰላ ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ብቻ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታውን ሙሉ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 80 አራተኛ ፎቅ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የገዛውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለበትን ክፍሎች በሙሉ የመሙላት ማህተም አድርጎ ሙሉውን ሰነድ ማስገባት ይኖርበታል ይህን ያላደረገ ተጫራች በቅድመ ጨረታ ልየታ ውድቅ እንደሚሆን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
  4. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
  5. ተጫራቾች በሰነዳቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የቴክኒካል ስፔሲፊኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በቅጂ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት አስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ አራኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 80 ግዥ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት እንዲሁም የገዙትን የጨረታ ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ የስብሰባ አዳራሽ 3:30 የሚከፈት ይሆናል።
  10. ተቋሙ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በሚዋዋልበት ጊዜ 20% የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. የህክምና መሳሪያ ላይ የምትጫረቱ ተጫራቾች የምታቀርቡትን እቃ እስፔሺፊኬሽን ማቅረብ እንዲሁም ለምታቀርቡት ዕቃ ቢያንስ የ2 ዓመት ጋራንት እንዲሁም መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች የአገልግሎት ዘመናቸው ቢያንስ ከ2 ዓመት በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነት ከተገለፀ ከ7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ

ኮልፌ አጠና ተራ ከፖሊስ ጣቢያው ከፍ ብሎ

ስልክ ቁጥር፡- 011-273-88-55   011-280-10-21 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender