የሰ/ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በአፈ/ተከሳሽ ወ/ሮ ደስታ አሰፋ ወል ብርሀን አስፋ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ለአፈፃፀም መነሻ የሆነው በላሊበላ ከተማ ደብረሲና ቀበሌ በአፈ/ተከሳሽ ወ/ሮ ደስታ አሰፋ ስም በካርታ ቁጥር 00281/2012 ተመዝግቦ የሚገኘው የንግድ ቤት እና ቦታ በመጀመሪያ ጨረታ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
North Wollo Zone High Court (የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት)
የመጀመሪያ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ ከሳሽ ------------ 1ኛ ተማሪ ናትናኤል አሳምነው
2ኛ/ ተማሪ ዳዊት አሳምነው ወ/ል የሸአለም ስብሀት
3ኛ/ ተማሪ ሳምኦን አሳምነው
4ኛ/ ማህሌት አሳምነው ወ/ል ደስታ አሰፋ
እና
በአፈ/ተከሳሽ ወ/ሮ ደስታ አሰፋ ወል ብርሀን አስፋ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ለአፈፃፀም መነሻ የሆነው በላሊበላ ከተማ ደብረሲና ቀበሌ በአፈ/ተከሳሽ ወ/ሮ ደስታ አሰፋ ስም በካርታ ቁጥር 00281/2012 ተመዝግቦ የሚገኘው፡-
በሰሜን –6 ሜትር መንገድ በደቡብ – እታገኝ አድማሱ በምስራቅ –ወዳጄ ውቡ በምዕራብ—12 ሜትር መንገድ የሚያዋስነው የንግድ ቤት እና ቦታ በመሆኑ መካፈል የማይችል እና በጋራ እነ ብሎ ሳይት ለማውጣት ግራ ቀኙ ያልተስማሙ በመሆኑ በባለሙያ ተገምቶ በቀረበው የቀጠና ዋጋ ብር 9,821,467.8 /ዘጠኝ ሚሊዩን ስምንት መቶ ሀያ አንድ ሺህ አራት መቶ ስልሳ ሰባት ብር ከስምንት ሳንቲም/ መነሻ ዋጋ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 423 መሰረት በመጀመሪያ ጨረታ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ስለዚህ የጨረታው ማስታወቂያ ከጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር በአየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ ይካሄዳል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ /መግዛት/ የሚፈልግ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መግዛት /መጫረት/ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን 25% ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ያለበት መሆኑን እናሳውቃለን።
የሰ/ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
