በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ Truck Tractor with trailer (minimum 40 Tons or 35 m³ capacity ۲۶) ብዛት አራት ከመጋዝን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የጨረታ ማስታወቂያ የሀገር ውስጥ ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ /01/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ Truck Tractor with trailer (minimum 40 Tons or 35 m³ capacity ۲۶) ብዛት አራት ከመጋዝን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው (የ2017/18 ዓ.ም)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ በታክስ ከፋይ የሆኑ እና የታክስ ክሊራንስ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 432- 3- 8 ከሚገኘው የግዢ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 1,500,000.00 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዢ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ኅዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዢ መምሪያ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0114420216 0114420688 4 አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
