የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከታህሳስ 01 ቀን 2018 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ7 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም/ወይም ጥሬ እህል፣ የማጣፈጫ፣ ፉርኖ ዱቄት፣ የማገዶ እንጨት፣ ስኳር እና ሸቀጣሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 1
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከታህሳስ 01 ቀን 2018 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ7 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም/ወይም ጥሬ እህል፣ የማጣፈጫ፣ ፉርኖ ዱቄት፣ የማገዶ እንጨት፣ ስኳር እና ሸቀጣሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማህበራትም ሆኑ ግለሰብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያ ማሟላት አለባቸው።
- በንግድ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡ የግብር ከፋይነት (TIN NO) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የቫት ከፋይነት እንዲሁም የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የህግ ታራሚዎች ኮሚቴ የማረሚያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ እና ከዞኑ አቃቢ ህግ ቢሮ እንዲሁም ከዞኑ ገ/ኢ/ትብብር በሚወከሉ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስሪያ ቤቱ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- በበሰለ ምግብ አቅርቦት በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
- ጥሬ እህል ለማቅረብ ለምወዳደሩ የእህሉን ናሙና እና የምወዳደሩበትን አይነት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታው ያቅረቡትን ሀሳብ መቀየር ወይንም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት አንስቶ በ3 ቀን ውስጥ ማረሚያ ቤት በመቅረብ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ ጥራቱን የጠበቀና ለአንድ ሰው የሚሆን ማረሚያ ቤቱ ባወጣው ሜኑ መሰረት አቅርቦት መመገብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማረሚያ ቤት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳይን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውና የውል ማስከበሪያ በጥቃቅንና አነስተኛ ደንብ 192/2009 ተሻሽሎ በወጣው አንቀፅ 27 መሠረት ከአደራጁ ክፍል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በጥሬ ገንዘብ (በባንከ የተመሰከረለት CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውል ማስከበሪያ 10% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ምግቡ የሚዘጋጀው በመስሪያ ቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሆኖ በማብሰያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች የማረሚያ ቤቱ እንዳለ ሆኖ የጎደለውን ጨረታውን ያሸነፉ ማህበራት ወይም ግለሰብ የማሟላት ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ለማ/ቤቱ ለበላይ አካሎች ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 5 ቀን ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የደ/ም/ሸ/ዞን/ገ/ኢ/ልማት ትብብር ፅ/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-3-41-11-90/ 011-3-41-00-23
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት
