Tender Detail

Tender Details


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በ2018 ዓ.ም በዩኒሴፍ ትምህርት STEP ፕሮጀከት ለሚደገፉ ወረዳዎች ለሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ፓድ /ሞዲስ/፣ የውስጥ ሱሪ /ፓንት/ እና ሳሙና እንደዚሁም ለሚኒሚዲያ አገልግሎት የሚውል እስፒከር፣ ዲቫይደርና ፍላሽ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በ2018 ዓ.ም በዩኒሴፍ ትምህርት STEP ፕሮጀከት ለሚደገፉ ወረዳዎች ለሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ፓድ /ሞዲስ/፣ የውስጥ ሱሪ /ፓንት/ እና ሳሙና እንደዚሁም ለሚኒሚዲያ አገልግሎት የሚውል እስፒከር፣ ዲቫይደርና ፍላሽ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 01 የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ፓድ ሞዲስ/፣ የውስጥ ሱሪ /ፓንት/ እና ሳሙና

ሎት 02 አስፒከር ዲቫይደር እና ፍላሽ

በመሆኑም ተጫራቾች፣

1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያሳደሱ በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብርከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት እንደዚሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ብር 200 ( ሁለት መቶ) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት-1 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) እና ለሎት -2 20,000 (ሃያ ሺህ ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ በቼከ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 

5. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ወራቤ ከተማ ከልል ትምህርት ቢሮ ግዥና ንብረት አስ/ዳይሬከቶሬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 8:00 ታሽጎ በ8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

7. የውል ማስከበሪያ፣ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ7 ቀናት በኋላ ውሉን መፈረምና የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች ከፍያ በሚፈጸምበት የገንዘብ አይነት የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ አለበት፡፡

8. ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታው ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድሩ በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡

9. የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ብቻ ነው::

10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር 0467710688 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የማዕከሳዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት ትም/ቢሮ

Save Tender