Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የለሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ወይን አምባ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0914364932
  • Website
  • Deadline17 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security65,000 /ስልሳ አምስት ሺህ/ ብር
  • opening date2025-11-17 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Machinery , Rent , Construction Machinery , Construction Works

በአብክመ በደ/ወሎ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለለገሂዳ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት በወረዳው ስር ለሚገኙ ቀበሌዎች ማለትም አዋተል 02 ቀበሌ ከአራበር እስከ ግሽነት አፋፍ ለሚሠራው የመንገድ ሥራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የለሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ በደ/ወሎ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለለገሂዳ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት በወረዳው ስር ለሚገኙ ቀበሌዎች ማለትም አዋተል 02 ቀበሌ ከአራበር እስከ ግሽነት አፋፍ ለሚሠራው የመንገድ ሥራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የማሽን ኪራይ

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ማለትም፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የቲን ነምበር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል እና ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
  2. ተጫራቾች የማሽኑን ሞዴል ስሪትና አቅም እንዲሁም የሥራውን ዝርዝር ከጨረታ ሰነድ ላይማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎክ 1 ቁጥር 1 በብር 200 /መቶ ብር ብቻ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ 65,000 /ስልሳ አምስት ሺህ/ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ማሽን ሞዴል፣ የማሽኑ የፈረስ ጉልበት ማሽኑ የተሠራበት ዘመን እ.ኤ.አ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ፡፡
  6. የማሽኑ ኪራይ ክፍያ የሚጀምረው በለገሂዳ ወረዳ ቀበሌ ከሚገኘው ፕሮጀክት ሥራ ከጀመረበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡
  7. የኦፕሬተር እና ሌሎች የቅባት ወጪዎች እንዲሁም የሳይት ሰርቪስ አገልግሎት አሸናፊው ድርጅት ይሸፍናል፡፡
  8. ማሽኑ በብልሽት ምክንያት የሚቆም ከሆነ የቆመበትን ሰዓት በተከራይ አይታሰብም፣
  9. ተጫራቾች ማሽኖች የሚጠቀሙትን የነዳጅና ቅባት ወጪዎችን ይሸፍናል።
  10. ተጫራቾች የማሽኑ የመጓጓዣ ክፍያ ደርሶ መልስ የሚሸፍኑ መሆኑን
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/የሥራ ሂደት ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል ጨረታው የሚታሸገው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይታሸጋል፡፡ በተመሳሳይ ቀን በ4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  12. ጨረታው የሚወዳደረው በጥቅል ዋጋ ነው ማለትም ሁሉንም ማሽኖች ያላሟላ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ላይ በአካል የማይገኙ ከሆነ የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል
  14. ተጫራቾች ያሸነፈበትን ማሽን ሲያቀርቡ በስፔስፊኬሽን መሰረት መሆኑን በባለሙያ ተረጋግጦ የሚቀርብ መሆን አለበት ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ በ5 ቀናት ውስጥ ትክክለኛውን ማሽን መተካት አለበት፡፡
  15. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውለታውን በመውሰድ የውለታ ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፡፡
  16. የጨረታ ማሸጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
  17. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  18. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0914364932 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡
  19. የወረዳችን ከተማ ከደ/ወሎ ዞን ምዕራብ አቅጣጫ በ103 ኪ.ሜ ላይ ትገኛለች፡፡
  20. የተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ለተከታታይ 60 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የለሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

ወይን አምባ

 

Save Tender