Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ገቢዎች ቢሮ በ 2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

South Ethiopia Region Revenue Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ)


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ገቢዎች ቢሮ በ 2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት

  • በሎት 1/ የጽሕፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
  • በሎት 2/ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የኔት ወርክ ዕቃዎች
  • በሎት 3/ ሞተር ሳይክል
  • በሎት 4/ መጋረጃ ለቢሮ አገልግሎት እነዚህን ዝርዝር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ጨረታው የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፋ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችል
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /ለአስራ አምስት / ተከታታይ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ገቢዎች ቢሮ ቁጥር 9 ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት የሰነድ መግዣ ክፍያ በመፈፀም ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ /10,000/ አስር ሺ ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ መሰረት በመሙላት ኦርጂናልና ኮፒውን ለየብቻ ማሸግ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በታሸገው ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ማለትም ቅዳሜና እሁድን በዓላት ቀናት ሳይጨምር ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታ ከታወጀበት እስከ 16ኛው የሥራ ቀን 6፡30 ድረስ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 9 ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው 16ኛው ቀን በ6፡30 ሰዓት ወዲያውኑ ታሽጐ በዚያው ዕለት ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጉ ዕቃዎች መ/ቤቱ ባስቀመጠው ቀን ማቅረብ ግዴታ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡

የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ይህን ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ጨረታውን ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0916698994 / 0927069646 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ገቢዎች ቢሮ

 

Save Tender