በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጎፋ ዞን የቡልቂ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቡልቂ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ጽ/ቤት የቢሮ ግንባታ እና ግንባታ ሥራ ህጋዊ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ካለፈው ተጫራች ጋር ጠንከር ያለ ውል በመግባት ለማስገንባት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጎፋ ዞን በቡልቂ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጎፋ ዞን የቡልቂ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቡልቂ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ጽ/ቤት የቢሮ ግንባታ እና ግንባታ ሥራ ህጋዊ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ካለፈው ተጫራች ጋር ጠንከር ያለ ውል በመግባት ለማስገንባት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁ የጨረታ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እየጋበዝን የጨረታ መስፈርቶችን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
- በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡ ደረጃቸው GC/BC-6 እና ከዛ በላይ የሆኑ
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በ2018 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- ከሚመለከተው ከፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የአንድ ዓመት ታከስ ክሊራንስ /TAX CLEARANCE/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከአሰሪ መ/ቤት የተሰጠ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ ሁለት ሥራ አፈፃጸም ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የመልካም ሥራ አፈፃጸም የመጨረሻ ዙር ክፍያ ሰርተፍኬት፣ የጊዜያዊ ርክክብ ቨርቫል ወይም የመጨረሻ ርከከብ ቨርቫልና የሥራ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /CPO/ በጥሬ ገንዘብ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ ብቻ በመክፈል ከቡልቂ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አደራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ21 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በቡልቂ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ንባብና በሂሳብ ማስተካከያ ልዩነት 2% በላይና በታች መሆን የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በአካባቢ ውስጥ ሲሠሩ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጠባቸው መሆን አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0928977720/0943076288 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጎፋ ዞን የቡልቂ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
