በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት የጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ በቸሀ ወረዳ የኮይካ ውሃ ፕሮጀከት ፓምፕ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት የጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- 4/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት የጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ በቸሀ ወረዳ የኮይካ ውሃ ፕሮጀከት ፓምፕ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው፣
4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. የግዢው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም፣ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የፓምፕ ግዢ ብር 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመከፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
12. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡
13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-3-30-01-12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት እንገልፃለን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን
ውሃ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ
