Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-20 00:00:00
  • Categories Food Items And Drinks

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የታሸገ ውሃ፤ የዓሳ ስጋ የአትክልትና ፍራፍሬ፤ ግብአቶችን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 003/18

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የታሸገ ውሃ፤ የዓሳ ስጋ የአትክልትና ፍራፍሬ፤ ግብአቶችን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው። በዚህም መሰረት፣ ለግብር ዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ክሊራንስ ወይም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  • ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ከፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴከኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ/ የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይይውልና በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ8፡30 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይሆናል ።
  • ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍስ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከሳህሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፌት ስፌት የሚገኘው ህንፃ

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

Save Tender