በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኘው ወረዳው መንገድና ሎጂስቲክ ጽ/ቤት በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙትን መንገዶች ሕጋዊ የሆኑትን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሽነሪ በመከራየት ጠጠር መንገድ ጥገና ማሠራት ይፈልጋል
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በደሌ ዞን የዲዴሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኘው ወረዳው መንገድና ሎጂስቲክ ጽ/ቤት በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙትን መንገዶች ሕጋዊ የሆኑትን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግሬደር ( caterpillar 140-H) ፣ ዳምፕትራከ፣ እስካቫተር Dosan; ከ340 ፈረስ ጉልበት በላይ የሆነ፣ እስካቫተር cat ወይም hitachi; ከ340 ፈረስ ጉልበት በላይ የሆነ ሩሎ ባለ 12 ቶን cat ወይም liugong በመከራየት ጠጠር መንገድ ጥገና ማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች/ ኩባንያ ማሽን ለማከራየት የሥራ ፍቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች በጨረታው ለመወዳደር የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ወይም ከጉሙሩክ ባለሥልጣን ወይም ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ 15% ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተፈላጊ የማሸን /ተሽከርካሪ /ዓይነት ከ2018 ወዲህ የተሠራና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም ከማሽን አከራይ ድርጅት ሕጋዊ ወክልና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች; /ተወዳዳሪ/ ድርጅት የሥራ ልምድ ያለውን ኦፕሬተር ማቅረብ የሚችልና ኦፕሬተሩ ችግር ከፈጠረ መቀየር የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በሥራላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ካሉ /የማሽኑ/ የተሽከርካሪው / ጥገና ወጪ በራሳቸው ለመሸፈን ዝግጁ የሆኑ።
- መ/ቤቱ ለማሠራት ካወዳደረው መንገዶች ውስጥ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የማሠራት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተወዳዳሪ አሸናፊ ለሥራው የሚያስፈልጉትን ነዳጅ፣ ዘይት፣ ግራሶና ሌሎችንም ወጪዎች ራሳቸው ለመሸፈን ፈቃደኛ የሆኑ።
- ተጫራቾች /የማሽኑን/ ተሽከርካሪውን ጭነው ማቅረብና ከሳይት ሣይት በራሳቸው ወጪማጓጓዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በ10 ቀናት ውስጥ /የማሽኑ/ የተሽከርካሪውን ወደሥራ ቦታ ለማስገባት ዝግጁ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ካሁን በፊት በዚህ ዓይነት ሥራ ላይ ተወዳድረው አሸንፈው ከሠሩበት መ/ቤት ከአንድ ዓመት ወዲህ የተሰጣቸውን የሥራ ጥራት የምስክር ወረቀት /የሥራ ልምድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጫራቾች /የተወዳዳሪዎች/ ዋጋ ወይም ውጤት ተቀባይነት የሚያገኘው የተጠቀሱት ተፈላጊ ማሽኖች ጠቅላላ ዋጋ ተደምሮ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተወዳዳሪ አሽናፊ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ብር 50,000(ሀምሳ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታው ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ውል ሰምምነት ለመፈጸም ዘግጁ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ማሽን በቂ ፐርፎርማንስ ሊኖረው የሚገባ መሆን አለበት፡፡ ከሚጠበቀው /standard/ በታች ከሆነ በሌላ ለመተካት ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ቴክንካል፣ ኦሪጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒ በማሽግ የሚመለከተውን የድርጅቱን ኃላፊ በማስፈረምና ሕጋዊ ማህተም አድርገውበት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጨረታ ሣጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ውስጥ የጨረታውን ሠነድ ከዲዴሣ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው የሥራ ቀን በ11/3/2018 ዓ.ም በ6፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 20 36 03 88 / 09 13 37 42 37 ሁሌ በሥራ ሰዓት መደወል ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በደሌ ዞን የዲዴሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
