የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከሕጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 03/2018
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከሕጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ለጨረታ የቀረቡ እቃዎችም።
- ሶዴም ሃይፖ ክሎራይት 10%፣
- ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ፣
- ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ፣
- የጽሕፈት መሣሪያ፣
በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ለመመዘገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ፤ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት /በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፣
- ድርጅቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽንና ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅርብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፖስታ በማድረግ ዘወትር በሥራ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደማ/ከ/ውሃ/አገ/አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የሥ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጪ አያስደርግም፡፡
- በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ መ/ቤቱ አይሸፍንም፡፡
- ተጫራቾች የሚፈፅሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ደ/ማ/ከ/የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 058-7-71-68-40/ 058-7-71-10-58/ 058-7-71-15-20
ማሳሰቢያ፡-
- ኬሚካሉ በየወሩ ተከፋፍሎ በዓመቱ ውስጥ የሚመጣ መሆኑ ይታወቅ፡፡
- የቧንቧና መገጣጠሚያ እቃዎች ድርጅቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት የእቃ ናሙናውን እንድታዩ እያሳሰብን፣ የእቃውን ፎቶ ግራፍ አይታችሁ ዋጋ የምትሞሉ ፎቶ የእቃውን አይነት እንጅ የእቃ ጥራትን ስለማያሳይ በአካል መጥታችሁ ናሙናውን እንድታዩ እናስታውቃለን፡፡
- ርክክቡ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
