በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በዳውሮ ዞን የከጪ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከጪ ወረዳ ውሃ ማ/ኢ/ል/ጽ/ቤት፣ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤትና ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በኩል በወረዳችን ውስጥ በተለያዩ ቀበሌያት በCOWASH PROGRAM የሚሠሩትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የሕንፃና ዘመናዊ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በዳውሮ ዞን የከጪ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በዳውሮ ዞን የከጪ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከጪ ወረዳ ውሃ ማ/ኢ/ል/ጽ/ቤት፣ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤትና ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በኩል በወረዳችን ውስጥ በተለያዩ ቀበሌያት በCOWASH PROGRAM የሚሠሩትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የሕንፃና ዘመናዊ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የግንባታ ዓይነት |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ደረጃ |
የበጀት መ/ቤት |
|
1 |
የከጪ ቱታ ቀበሌ ቱታ 1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት MHM ግንባታ ፕሮጀክት |
ሎት-1 |
8,500 ብር |
ቢሲ/BC-8/GC/ጂሲ-8ና ከዚያ በላይ |
ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት |
|
2 |
የከጪ ቱታ ቀበሌ ቱታ 1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት መምራን መፀዳጃ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት |
ሎት-2 |
8,000 ብር |
ቢሲ/BC-8/GC/ጂሲ-8ና ከዚያ በላይ |
ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት |
|
3 |
የከጪ ቱታ ቀበሌ ቱታ 1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት የወንድ ተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት |
ሎት-3 |
8,000 ብር |
ቢሲ/BC-8/GC/ጂሲ-8ና ከዚያ በላይ |
ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት |
|
4 |
የከጪ ቱታ ቀበሌ ቱታ 1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት |
ሎት-4 |
8,000 ብር |
ቢሲ/BC-8/GC/ጂሲ-8ና ከዚያ በላይ |
ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት |
|
5 |
የሾጋ ባላ ቀበሌ ሾጋ ጤና ከላ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት |
ሎት-5 |
9,000 ብር |
ቢሲ/BC-8/GC/ጂሲ-8ና ከዚያ በላይ |
ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት |
|
6 |
የማልጋ ማራጫ ቀበሌ ማልጋ ጤና ከላ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት |
ሎት-6 |
9,000 ብር |
ቢሲ/BC-8/GC/ጂሲ-8ና ከዚያ በላይ |
ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት |
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰፈርት መሠረት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin NO/፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ የቫት/ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢ፤
- በወረዳችን ውስጥ ከዚህ በፊት በእጁ ምንም የግንባታ ሥራ የሌለ በወረዳችን ውስጥ የግንባታ ሥራ ሠርተው ከሆነ የወረዳችን መልካም ሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በወረዳችን ውስጥ ከዚህ በፊት በውሉ መሠረት ግንባታ ሥራን ያልጨረሱ እና በማህበር ሆነው የግንባታ ሥራን በተለያዩ ምክንያቶች በውሉ መሰረት ያልጨረሱ የማህበር አባላት በግል የግንባታ ንግድ ሥራ ፍቃድ ቢያወጡም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም ፡፡
- ተጫራቾች በፕሮግራም ዘርፍ የሕንፃና ዘመናዊ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራን በውሉ መሠረት ሠርቶ መጨረሱን የሚገልጽ 3 /ሦስት/ና ከዚያ በላይ መልካም የሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ማቅረብ ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መልካም የሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ግንባታ ውል የገቡበትን ወረቀት ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ እና ተጫራቾች ከዚህ በፊት በወረዳችን ውስጥ በፕሮግራሙ ዘርፍ የሠሩ ከሆነ የወረዳችን መልካም ሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ለማለፍ በቴክኒካል ግምገማ ላይ 70%ና ከዚያ በላይ የሆነ ውጤት ማምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው በግንባታ ሥራ ላይ የግንባታ የግንባታ ቦታ ጉብኝትን የሚገልጽ ማስረጃ ከከጪ ወረዳ ውሃ/ማ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚህ ግንባታ ተብሎ ከተመደበው ከባለድርሻ አካል ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ላሸነፉበት ለግንባታ ሥራ የሚሆነውን የግንባታ ዕቃዎችን /ግብዓቶችን/ በራሱ ወጪ መስገባት የሚችሉ።
- ተጫራቾች አሻሚና ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ የጨረታ ዋጋ በመሙላት መወዳደር/ለመወዳደር መሞከር ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 21 በሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ-04 በመቅረብ ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጀውን ለየብቻ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ይህ ጨረታ በማስታወቂያ በወጣበት በ22ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በእለቱ 8፡30 ይከፈታል፤ የመክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ሥራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጉልም፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ጨረታ ላይ የቴክኒካልና ፋይናንሻል ጨረታ ሰነድ ኦሪጂናሉን ለየብቻ በፖስታ አሽገው በአንድ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና የኦሪጂናሉን አንድ ፎቶ ኮፒ በፖስታ አሽገው የሚያስፈልገውን አድራሻና የግንባታ ዓይነት በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ጨረታ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ የተረጋገጠ CPO /Bid bond/ ቼክ/ ጥሬ በከጪ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም አሠርቶ ማቅረብ የሚችሉ። ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግዎ በስ.ቁ 0912456179 /0937962147/0968538319 ይደውሉ።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በዳውሮ ዞን የከጪ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
