የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች መለዋወጫ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የተለያዩ የተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች መለዋወጫ መነሻ ዋጋ
በማስቀመጥ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች መለዋወጫ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መስፈርት የማከበርና የመፈፀም ግዴታ አለባቸው፡፡
1. ይህ ጨረታ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሊሳተፍበት ይችላል፡፡
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉቀን እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ባሉት የሥራ ቀናት ከ3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት ከ 7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ቃሊቲ ግቢ (ቃሊቲ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ የመለዋወጫ ግምጃ ቤት) በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
4. አንድ ተጫራች የተለያዩ የማሽነሪ እና የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዓይነታቸውን መሰረት በማድረግ የሚገዛበትን የአንድ ዋጋ እና ጠቅላላ የሚገዛውን መጠን በማስገባት መጫረት ይኖርበታል፡፡
5. የዚህ ጨረታ ከተቀመጠው መነሻ ዋጋ በታች መጫረት አይቻልም፡፡ ከመነሻ ዋጋ በታች ያስገቡ ተጫራቾች በቀጥታ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ሲገዙ ትክከለኛ አድራሻቸውንና ሥማቸውን በመግለጽ ፈርመው መውሰድ አለባቸው::
7. ጨረታው ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው (በዕለቱ) በ 4:30 (አራት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
8. ኢንተርፕራዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመታወቂያ እና የጨረታ ሠነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለሽያጭ የቀረቡት የተለያዩ ዓይነት መለዋወጫዎች፡-
1. Lining
2. Gasket
3. Iveco
4. Mercedes
5. Concrete Pump
6. Air Compressor
7. Dumper
8. Scania
9. Others
10.North Benz
11.Dong Fing
12.Cat
13.Komatsu
14.Hoynday
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርኘራይዝ ቃሊቲ ግቢ ስልክ ቁጥር
011-4-40-34-34 ማዞሪያ 011-4-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ info@dce-et-com
የድረ-ገጽ አድራሻ WWW.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ. 3414 114-40-40-71/0114-420746
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርኘራይዝ
