Tender Detail

Tender Details

  • Company ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር
  • Address ቦሌ ካርጎ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0965683654
  • Website
  • Deadline07 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-07 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Industry And Factory

ሐበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅት/ቶች በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት/ቶች ጋር ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር ለማቅረብ ተፈራርሞ መስራት ይፈልጋል።

ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር


 

ሐበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር

“ነጭ የተጣራ ስኳር'' ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ሐበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅት/ቶች በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት/ቶች ጋር ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር ለማቅረብ ተፈራርሞ መስራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  • ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ፤ ለምግብ እና መጠጥ ምርት ተስማሚ የሆነ ነጭ የተጣራ ስኳር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ስኳሩ ከብክለት የጸዳ መሆኑን፤ ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫዎችን የተከተለ እና እርጥበትን መቋቋም በሚችል ማሸጊያዎች መታሽጉን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
  • 4 ሚሊየን ኪሎ (4000 ቶን) ስኳር ማቅረብ መቻል ይኖርባቸዋል።
  • በስራ ላይ ምንም አይነት መስተጓጎል አለመኖሩን ለማረጋገጥ በቅድመ-ስምምነት መሰረት ስኳሩን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
  • ንጽህና፤ የእርጥበት መጠን እና ጎጂ ንጥረ ነገሮች አለመኖር ያሉ የጥራት መለኪያዎችን ለማረጋገጥ ለእያንዳንዱ ባች የትንታኔ ሰርተፍኬት (certificate of Analysis) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ጉድለት ያለባቸውን አቅርቦቶችን ያለምንም ተጨማሪ ወጪ መተካት ይኖርባቸዋል።
  • በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት፣ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  • ተጫራቾች ወደዋና መስርያ ቤት በመምጣት እስከ ጥቅምት 28 ሰባት ሰአት ድረስ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መቀበል ይኖርባቸዋል። ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 28 ስምንት ሰአት ድረስ ተጫራጮች በአካል ዋና መስርያ ቤት በመገኘት ወይም በኢሜል አድራሻ factoryprocurement@habeshabreweries.com መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ድርጅቱ ምላሾቹ ከተቀበለ በኋላ የጨረታ ሰነዶችን በመገምገም የተመረጡትን / ያሸነፉትን አቅራቢዎችን ያሳወቃል።

 

አድራሻ፡ ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር

ቦሌ ካርጎ ፊት ለፊት

ስ.ቁ 0965683654/0911478704

አዲስ አበባ ፣

ኢትዮጵያ

 

Save Tender