በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በመንግሥት የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ብቁ ተጫራቾችን እንዲሳተፉ ይጋበዛል፡፡
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታ መሳተፉ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡብት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት በመ/ቤታችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000322276919 የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ዘውትር በሥራ ሰዓት ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ባለው ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ ያያዘውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን 400,0000 (አራት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የቴክንኩን እና ፋይናንሻሉን ሠነድ በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ ለተከታታይ 15 ቀናት በሥራ ሰዓት ከሰኞ-ዓርብ ከመታሸጉ በፊት በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡20 ተጫራቾ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የሚያቀርቡት ጎማዎች ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጎማዎች ባለሽቦ ሆኖ ዓይነቱን መጥቀስ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-551-1292 ይደውሉ።
ፖ/ሳ/ቁጥር 116
አድራሻ፡- ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሱ ጎፋ ማዞሪያ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
