Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251910120628
  • Website
  • Deadline07 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-11-07 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Metals And Metal Working , Vehicle tire

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያየ ሳይዝ ያላቸው የቀላል ተሽከርካሪ እና የከባድ ማሽነሪ ጎማዎች፣ ዮፕላሲቲክ ቦቲ ጫማዎችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)


 

አንደኛ ዙር የወጣ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አሽጩ/001/ኦኩስፋ/1እና3/2018

 

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያየ ሳይዝ ያላቸው የቀላል ተሽከርካሪ እና የከባድ ማሽነሪ ጎማዎች፣ ዮፕላሲቲክ ቦቲ ጫማዎችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ህጋዊ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ፡- ክልል በምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እና ክልል ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ወረዳ ሳላማጎ ወረዳ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ነው።
  3. ጨረታው ጥቅምት 28 ቀን /2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 28/02/18 ዓም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በሃርድ ኮፒ እና 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በሶፍት ኮፒ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ከታች በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. ለሽያጭ የቀረቡ እቃዎች ወይም ንብረቶችን ዝርዝር የያዘው መደበኛ የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት፤ የመወዳደሪያው ሰነድ የሚገባበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ፡- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር -1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ስልክ ቁጥር 09-10-12-06-28 እና 09-13-54-47-31 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ፤
  6. ተጨማሪ የጨረታ ሰነድ ለመሸጥ ብቻ የሚያገለግል የሻጭ አድራሻ ኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር-1 እና 3 ስልክ ቁጥር 09-16-170834 ኩራዝ፤
  7. ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀመው ቦታ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር - 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
  8. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ብቁ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል ዕቃዎች ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡-
  • ጥቅል-1 (ሎት-1) የተሽከርካሪ የጎማ ሽያጭ ብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ ብር)
  • ጥቅል-1 (ሎት-2) የፕላስቲክ ቦቲ ጫማ ሽያጭ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • ጥቅል-1 (ሎት-3) ቁርጥራጭ ብረቶች ሽያጭ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  1. ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀመው ቦታ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
  2. ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት ነው፡፡

 

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ

 

Save Tender