በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ትራንስፖርት (ፑሚስ፣ ክሊንከር፣ ጅፕሰም) እና ሲሚንቶ የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በግልፅ የሀገር ውስጥ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሰፋ/Re-58/2017
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ትራንስፖርት (ፑሚስ፣ ክሊንከር፣ ጅፕሰም) እና ሲሚንቶ የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በግልፅ የሀገር ውስጥ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የታደሠ ንግድ ፍቃድ ያላቸው (የ2017/18 ዓ/ም) ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ እና የታክስ ክሊራንስ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እያቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.RO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒከ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ 011 442 0216 /ፋክስ 011 442 0688
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
