የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መመሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመስኩ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ከዚህ በታች በሎት 1 እና በሎት 2 የተዘረዘሩትን ዕታዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ግልጽ 01/2018
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መመሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመስኩ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ከዚህ በታች በሎት 1 እና በሎት 2 የተዘረዘሩትን ዕታዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።
የዕቃ አይነት፡-
- ሎት 1 - አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 2 - ኤሌክትሮኒክስ
በዚሁ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ሁሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መሳተፍ ይችላሉ።
- ከላይ በተጠቀሱት ለመወዳደር በየዘርፍ ሥራዎች የተሰማሩ፤ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በገቢዎች ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 እና 2 በብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
- ተጫራች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በቢሮ ቁጥር 02 ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርቦ የጨረታ ሠነዱን የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን አሪጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ኤንቨሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታ ሳጥኑም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16 /አስራ ስድስተኛው/ የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካሉና ፋይናንሻሉን በተለያዩ ኤንቨሎፕ ከታሸገ በኋላ በአንድ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማሸግ አለባቸው። በዕለቱ ቴክኒካሉን ክፍል ብቻ ይከፈታል።
- የጨረታ ሳጥኑም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16 /አስራ ስድስተኛው/ የሥራ ቀን በ4:00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል።
- ይህ ጨረታ ከተሞላበት ቀን ጀምሮ ዋጋ የሚፀናበትን ከ45 ቀናት በታች የጊዜ ገደብ መስጠት የለበትም።
- ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሮ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮው ጨረታውን የሚከፍት መሆኑን ይገልጻል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ7 ቀናት በኋላ ቀርቦ ውሉን መፈረም ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እያንዳንዳቸውን እቃ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ቢሮ ድረስ በማቅረብ በተፈለገው/ በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሆኑን በባለሙያ ከተጣራ በኋላ ማስረከብ አለበት፡፡
- አቅራቢው የውል ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ ክፍያው ወዲያውኑ በቼክ ይከፈለዋል።
- አቅራቢው የውል ግዴታውን ሙሉ በሙሉ አለመፈፀሙ ሲረጋገጥ በውል ግዴታው መሰረት በህግ አግባብ ይቀጣል።
- ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት ዳይሬክቶሬት
የስልክ ቁጥር-09-16-03-70-38
አድራሻ፡- ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ህንጻ ውስጥ (ሀዋሳ)
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
