Tender Detail

Tender Details

  • Deadline15 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ)
  • opening date2025-11-15 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ሰነድ

የጨረታ ቁጥር፡- PPS/NVP-4FBI/03/02/2018

 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በጨረታው ላይ የሚወዳደሩት በማዕድን ሚኒስቴር የተለዩ የብረት አቅላጭ የግል ድርጅቶች የሆኑና የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉ ናቸው።
  2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የብረቶቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ በቴሌ ብር እና ሲቢኢ ብርን በመጠቀም የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከ3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብረታ ብረቶቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) ዋስትና ያላስያዘ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።
  5. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  6. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒአ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል። ይሁንና የብረታ ብረቶቹን ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ዋስትና ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟለ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
  7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ብረታ ብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች ያሸነፉትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ብረታ ብረቱ ከሚገኝበት ስፍራ ቅርብ በሆነ ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ውል በፈረሙ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቱን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው።
  11. ግምታዊ መጠኑ ከፕሪንት አውት ከሚገኘው ትክከለኛ የብረቱ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ልዩነት የሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን በትርፍነት የሰጠው ተመላሽ የሚደረግለት ገንዘብ ካለም በአገልግሎቱ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።
  12. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
  13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  14. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ወይም ሌላ ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምከንያት ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቅ ነው።

 

አድራሻ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ የተቋማችንን ድረ-ገጽ፡- www.pps.gov.et ይጎብኙ

 

የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት

 

 

Save Tender