በአማራ ገጠር መንገዶች ከንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት /ደብረ ብርሃን/
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
በአማራ ገጠር መንገዶች ከንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁትን መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው።
- የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትከክል የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለውሃ ቦቴ በሰዓት፤ ለገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ እና ሎቤድ በኪ.ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000143426525 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናሉን ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጥግና ጽ/ቤቱ ደ/ብርሃን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሞሉትን ዋጋ /ሰነዳቸውን/ በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ አፈሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጥገና ጽ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 011-681-38-85 በመላክ ወይም ቁጥር 011-681-30-66 ወይም 0913189073/0987634263 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት /ደብረ ብርሃን/
