በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለከላላ ከተማ አስተዳደር ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፤ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃ፤ ሎት 3 የጽዳት እቃ፤ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ እቃ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለከላላ ከተማ አስተዳደር ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፤ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃ፤ ሎት 3 የጽዳት እቃ፤ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ እቃ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1–4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 (ደረሰኝ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለእያንዳንዳቸው ሎቶች ለየብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር በሎት ወይም በተናጠል ሊሆን ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከገቢዎች ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከለላ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0914361759/0945488842 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ የሚያቀርቧቸው እቃዎች በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ እና ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊነታቸው ከታወቀ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በከለላ ወረዳ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል መግባት አለባቸው እቃውንም ከዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ ስፔር ፓርት ውጭ በከለላ ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ት/ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዘው ማምጣት አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከለላ ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለ ጀምሮ በሚቆይ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከለላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዢ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ጊዜ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የእቃውን 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
