የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ በክልሉ ውስጥ ለሚሰራው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከለሚ ናሽንል ሲሚንቶ ፋብሪካ በክልሉ ውስጥ ባሉ ከተሞች ማለትም ባህር ዳር፣ ደ/ማርቆስ፣ አዘዞ፣ ደ/ታቦር፣ ወልዲያ፣ ደሴ እና ደ/ብርሃን ከተሞች ለማጓጓዝ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የማጓጓዝ አገልግሎት ግዥዉን መፈጸም ይፈልጋል፡፡
Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 09/2018 ዓ.ም
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ በክልሉ ውስጥ ለሚሰራው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከለሚ ናሽንል ሲሚንቶ ፋብሪካ በክልሉ ውስጥ ባሉ ከተሞች ማለትም ባህር ዳር፣ ደ/ማርቆስ፣ አዘዞ፣ ደ/ታቦር፣ ወልዲያ፣ ደሴ እና ደ/ብርሃን ከተሞች ለማጓጓዝ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የማጓጓዝ አገልግሎት ግዥዉን መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 13 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጀዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በኮንስትራክሽን ኤጀንሲው አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ17/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 02/03/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሲሚንቶ ማጓጓዝ ስራውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ አሪጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ17/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 02/03/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትንና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ አፊሰሮች ቢሮ በቀን 02/03/2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-2-22-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-3-22-05-155/058-2-22-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲዉ ድረ-ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
ፖ.ሣ.ቁ 382
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
