የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2018 ዓ.ም በታቀደው መሠረት ለከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ለከተሞች ፎረም አገልግሎት የሚውሉ Led screen ኪራይ እና የመግቢያ በር /Entrance get way ለማሰራት ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2018 ዓ.ም በታቀደው መሠረት ለከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ለከተሞች ፎረም አገልግሎት የሚውሉ Led screen ኪራይ እና የመግቢያ በር /Entrance get way ለማሰራት ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚገዙ ዕቃዎች -
- ሎት/ምድብ Led screen ኪራይ
- ሎት/ምድብ የመግቢያ በር/Entrance get way ለማሰራት
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ስነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛዉቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 4፡00 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
