በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአንኮበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአንኮበር ወረዳ ላይ ለሚገኙ አጠቃላይ ሴ/መ/ቤቶች ለ2018 የበጀት ዓመት ለስራ እንቅስቃሴ የሚያስፈልጋቸውን ከዚህ በታች ባሉት የተዘረዘሩ ግዥዎችን በሎት በማደራጀት በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአንኮበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአንኮበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአንኮበር ወረዳ ላይ ለሚገኙ አጠቃላይ ሴ/መ/ቤቶች ለ2018 የበጀት ዓመት ለስራ እንቅስቃሴ የሚያስፈልጋቸውን ከዚህ በታች ባሉት የተዘረዘሩ ግዥዎችን በሎት በማደራጀት በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና ጫማዎች፣
- የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች፣
በዚህ መሰረት-
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሀጋዊ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፣
3. የግዥው መጠን በአንድ ሰነድ ላይ ብር 200.000 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታችውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሶነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአንኮበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 50/ ሃምሳ ብር/ በመከፈልና ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላል፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከ1% የማያንስ በጥሬ ገንዘብ ወይም በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ወይም በባንክበተረጋገጠ ቼከ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፣ ሲፒአ የሚያቀርቡ ከሆነ የአንኮበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት ተብሎ ካልመጣ ቢድ ቦንዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
7. የጨረታ ሰነድ የሚገባው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ የካላንደር ቀናት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በጥሩ ሁኔታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ እና የሚወዳደሩበትን የግዥ የሎት አይነት በመግለፅ አንኮበር ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው::
8. የጨረታው የመጨረሻ ማስገቢያ ቀን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ነው፡፡
9. ጨረታው የሚከፈተው በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ወይም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ የመከፈቻው ቀን በስራ ቀን ላይ የማይውል ከሆነ በቀጣይበሚመጣው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
10. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊው ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
12 ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
13. በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ ድርጅቶች በጨረታው ያሸነፈባቸውን እቃዎች አ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በየንብረት ከፍሎቹ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
14. አሸናፊ የሚሆኑ ድርጅቶች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች እንደ አስፈላጊነቱ በቅድሚያ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-6-23-01-77/ 011-6-23-01-37 ደውለው ይጠይቁ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአንኮበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
