በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን በሀ/ማ/ከሰም ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ የፅህፈት መሳሪያ ፣ የፎቶ ኮፒ ጥገና ፣ የደንብ ልብስና ጫማዎች፣ ብትን ጨርቆች፣ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎችና መሳሪያዎች፣ ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች የቢሮ ጥገና እቃዎች; መስተንግዶ አቅርቦት እና ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ ፍርድ ቤት ሾላ ገበያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን በሀ/ማ/ከሰም ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ የፅህፈት መሳሪያ ፣ የፎቶ ኮፒ ጥገና ፣ የደንብ ልብስና ጫማዎች፣ ብትን ጨርቆች፣ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎችና መሳሪያዎች፣ ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች የቢሮ ጥገና እቃዎች; መስተንግዶ አቅርቦት እና ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስስዚህ ተጫራቾች
1. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፡፡
3. የግዥው መጠን ብር / 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /Tax/ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የሚገዙ እቃዎችን አይነት ፣ብዛትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፌክሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20 ብቻ በመከፈል ከግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሰ..ፒ.ኦ./ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መ/ሂ 1 ማስያዝ ይችላሉ፡፡
8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሀ/ማ/ከሰም ወረዳ ፍርድ ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፣ የጨረታ ሳጥኑ11፡31 ይታሸጋል፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4.00 ሰዓት ይከፈታል። 16 ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4.00 ሰዓት ይከፈታል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 0116191024 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፦ ከአዲስ አበባ ወደ ደ/ብርሃን በሚወስደው አስፋልት ከሸኖ ከተማ አለፍ ብሎ ወደ ምስራቅ 39 ኪ.ሜ ገባ ብሎ እንገኛለን።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰሜን ሸዋ ዞን የሀገረ ማሪያም ወረዳ ፍርድ ቤት
