Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ አካባቢ በሚገኛው አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ህንፃ 15ኛ ፎቅ የሰፕላይ ቼይን እና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-38-98
  • Websitehttp://www.ethiopianelectricutility.gov.et/
  • Deadline04 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-11-04 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Merchandise

ተቋማችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለክበብ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግብዓት ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢኤስ/47/7ጨ007/2018

 

ተቋማችን ለክበብ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግብዓት ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል።

 

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

የጥራ ጥሬ ግብዓት አቅርቦት

30,000.00

ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ    8፡00 ሰዓት

ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

2

የወተት ተዋፅኦ እና ቅመማ ቅመም ግብዓት አቅርቦት

30,000.00

ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ    8፡00 ሰዓት

ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
  3. አድራሻ፡- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋና መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ ፍሊትና ፋሲሊቲ ገዥ ክፍል ስልክ ቁጥር 011-1-56-01-48።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና "ETHIOPIAN ELECTRIC UTILTY" በሚል መሆን ይኖርበታል፣
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረገ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  7. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

 

Save Tender