በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከለኛ አውቶብሶች (Medium Bus) ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/08/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከለኛ አውቶብሶች (Medium Bus) ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ፣ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች medium-bus (መካከለኛ አውቶብሶች) ግዥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/08/2018 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
መካከለኛ አውቶብሶች (medium-bus) ግዥ |
ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) |
ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ።
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
