Tender Detail

Tender Details

  • Company የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 222 14 79
  • Website
  • Deadline05 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው መጠን በዕጣ ይለያያል።
  • opening date2025-11-05 00:00:00
  • Categories Machinery , Machinery , Vehicle , Vehicle

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር በሚገኘው ቢሯችን፡ ኮምቦልቻ እና አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚገኙትን ያገለገለ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች እንዲሁም መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች እንዲሁም መለዋወጫዎች ሽያጭ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ግ/ጨ/ቁጥር 45/2018

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር በሚገኘው ቢሯችን፡ ኮምቦልቻ እና አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚገኙትን ያገለገለ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች እንዲሁም መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች የሚሸጡትን ያገለገለ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች እንዲሁም መለዋወጫዎች ዋናው ግቢ፣ ፕላስቲክ ፋብሪካ፣ ኮምቦልቻ እንዲሁም አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሚገኘው በአካል በመገኘት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት በመመልከት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይቻላል። መለዋወጫው የሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግቢ ውስጥ ነው።
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ። ነገር ግን በማህበር ለመወዳደር የሚፈልግ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ በፍትህ ተቋም የተሰጠውን ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን ቢሮ ቁጥር 02 ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /bid bond/ የተጨማሪ እሴት ታክስን 15% ጨምሮ የሚገዙበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በባንክ ማስያዥያ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ቼክ እንደ ማስያዥያ ማቅረብ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስያዣ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በከፈሉ ማግስት ጀምሮ እቃውን በ15 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው። ሆኖም ግን በተባለው ቀን የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት ሲፒኦ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ የሚያዋጣው ከሆነ 2ኛ ለወጣው ተጫራች የሚሸጠው ይሆናል።
  8. ጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000265163223 አስገብተው ማስረጃ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  9. ገዥው በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ እቃውን መረከብ ባይችል ያጋጠመውን ችግር ከበቂ ማስረጃ ጋር በጽሑፍ አመልክቶ የድርጅቱ የሚመለከተው ኃላፊ ሲፈቅድ ብቻ የርክክብ ጊዜው ሊራዘም ይችላል።
  10. የሚሸጡትን ያገለገለ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች እንዲሁም መለዋወጫዎች በተመለከተ ማንኛውም የጉልበት ሠራተኛ ወጭ እና የመጓጓዣ ወጭ አሽናፊው ድርጅት የሚሸፍን በመሆኑ በዚህ አግባብ ግዴታ የሚገባ ይሆናል።
  11. ለእያንዳንዱ እቃ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል።
  12. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን 09-67-44-22-04 እና 09-85-07-75-18 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender