Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ
  • Address ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር እልፍ ብሎ በቀድሞው የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና መ/ቤት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-01-95-69-26
  • Website
  • Deadline25 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2%
  • opening date2025-10-25 00:00:00
  • Categories Used Items

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ ዋና መ/ቤት ቄራ በሚገኘው ግቢ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001

 

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ ዋና መ/ቤት ቄራ በሚገኘው ግቢ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከዘርፉ ዋና መ/ቤት /አዲስ አበባ/ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2:30- 6:30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 11፡00 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በውድድሩ የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በEthiopian Trading Businesses Corporation Consumer Products Trade Business Unit (ETBC- IAPTU) ስም አስርቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመግዣ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን ይገባዋል፤ ከዚህ ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ብቻ ዋጋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ለሁሉም ዕቃዎች ዋጋ ማቅረብ አለባቸው። በከፊልም ሆነ በተናጠል ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፤ አሸናፊው የሚለየው ለሁሉም ዕቃዎች በቀረበ አጠቃላይ የዋጋ ድምር መሰረት ነው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ የሚሸጡ ያገለገሉ ንብረቶችን በዘርፉ ዋና መ/ቤት በአካል በመምጣት መመልከት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት በኋላ ሙሉ ክፍያ በመፈፀም ዕቃዎቹን በ7 ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው። በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ንብረቱን ካላነሳ ከ10ኛው ቀን በኋላ ላላነሳበት ለእያንዳንዱ ቀን በየቀኑ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡
  8. ዕቃዎቹን ለማንሳት የጉልበት ሰራተኞች፣ የማሽን እና የጭነት ተሽከርካሪ ክፍያዎች ካሉ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  9. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ቅጽ 002

የመግዣ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

ብዛት

የመግዣ ዋጋ

ከተ.እ.ታ በፊት (Before VAT)

ከተ.እ.ታ በኋላ (After VAT)

1

ያገለገለ የእንጨት ሸልፍ ትልቁ

10

 

 

2

የእንጨት ሸልፍ ትንሹ

14

 

 

3

ሙሉ ቆርቆሮ

25

 

 

4

ግማሽ ቆርቆሮ

200

 

 

5

የብረት ሸልፍ

12

 

 

6

ላሜራ

7

 

 

7

የብረት ካዝና

7

 

 

8

የተለያየ መጠን ያላቸው ጎረንዳዮ

100

 

 

9

የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር የብረት

1

 

 

10

የብረት በሮች

19

 

 

11

ያገለገሉ ተሸከርካሪ ወንበሮች

41

 

 

12

ያገለገሉ ልዩ ልዩ ቢሮ መገልገያ ወንበሮች

250

 

 

13

ያገለገሉ የእንጨት ወንበር

24

 

 

14

የተለያዩ ያገለገሉ ጠረጴዛዎች

55

 

 

15

የተበላሸ ዲጅታል ሚዛን

3

 

 

16

የካፍቴሪያ ባንኮኒ

3

 

 

17

ያገለገለ የፍራፍሬ ማስቀመጫ የፕላስቲክ ሳጥን /ካሳ/

3000

 

 

18

ያገለገለ ኤጋ ቆርቆሮ

44

 

 

 

 

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ

 

Save Tender