Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912 013 152
  • Website
  • Deadline19 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-19 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ክስ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የካ አባዶ ፕሮጀክት ሳይት 13 የሕንጻ ቁጥር 451፤ የቤት ቁጥር 17 የሆነ በአፈጸጸም ተከሳሽ ፈትለወርቅ ኃይሌ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ስፋቱ 57 ካ.ሜ የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት ግልጽ ጨረታ በማካሄድ በመሸጥ በቤቱ ላይ ያለው የባንክ ዕዳ ለባንክ ከተከፈለ በኋላ የሚቀረውን ገንዘብ ለግራ እና ቀኙ ማካፈል ይፈልጋል።

በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የፍርድ ባለመብቶች እነ ወ/ሮ ጽጌ አባይነህ 7 ሰዎች

 

የፍርድ ባለዕዳ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ኃይሌ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክስ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የካ አባዶ ፕሮጀክት ሳይት 13 የሕንጻ ቁጥር 451፤ የቤት ቁጥር 17 የሆነ በአፈጸጸም ተከሳሽ ፈትለወርቅ ኃይሌ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ስፋቱ 57 ካ.ሜ የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት በባለሙያ ተገምቶ በቀረበ መነሻ ዋጋ ብር 2,168,394 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና አራት) ግልጽ ጨረታ በማካሄድ በመሸጥ በቤቱ ላይ ያለው የባንክ ዕዳ ለባንክ ከተከፈለ በኋላ የሚቀረውን ገንዘብ ለግራ እና ቀኙ ማካፈል ስለተፈለገ የጨረታ ማስታወቂያ በከለቻ ኦሮሚያ እና አዲስ ዘመን ጋዜጦች ከ10/02/2018 ዓ.ም እስከ 10/03/2018 ዓ.ም. አየር ላይ በሚቆይ የጨረታ ማስታወቂያ በ13/03/2018 ዓ.ም. ከ3፡30 – 6፡30 ጨረታው የሚያካሄዱ ኮሚቴዎች በተገኙበት መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ጨረታ ላይ በመሳተፍ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች የቤቱን ዋጋ ግምት 1/4ኛ ከጨረታው ቀን አስቀድማችሁ በባንክ ሲፒኦ በማስያዝ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በጨረታ የሚሸጠው ቤት በሚገኝበት ኮንዶሚኒየም ግቢ በአካል በመገኘት ተወዳድራችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አዟል፡፡

ማሳሰቢያ

  1. በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ወይም በመወዳደር የቤቱን ዋጋ ግምት 1/4ኛ በሲፒኦ ተይዞ ለጨረታ ኮሚቴ መቅረብ አለበት
  2. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ገንዘብ ጨረታው ከተካሄደበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርበታል
  3. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ በጨረታ የሚሸጠው ቤት የሚገኝበት ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ
  4. የጨረታ ውጤት ለ15/03/2018 ዓ.ም 3፡30 ላይ ያቀርባል
  5. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912013152 እና 0911918247 ላይ በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ።

 

በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

 

Save Tender