Tender Detail

Tender Details

  • Company በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጎንደር ማተሚያ ድርጅት
  • Address ጎንደር ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-11-20-49-02
  • Website
  • Deadline07 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security1%
  • opening date2025-11-07 00:00:00
  • Categories Printed Advertising Materials

የጎንደር ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት ወረቀቶች፣ የህትመት ጥሬ እቃዎች እና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡ ፡

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጎንደር ማተሚያ ድርጅት


                                                                   የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት ወረቀቶች፣ የህትመት ጥሬ እቃዎች እና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡ ፡ ስለዚህ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይጠበቃል፡፡ 

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ 

  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ 

  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፣ 

  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣ 

  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-–4 የተጠቀሱትንና ሌሎች ጠቃሚ ናቸው የሚሏቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 

  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አዲስ አበባ ላለው ግዥ ሠራተኛ በስልክ ቁጥር 0913554466/0918082215 በመደወል ወይም ጎንደር ማተሚያ ድርጅት ዋናው መ/ቤት መላክ ይችላሉ፡፡ 

  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የገንዘብ መጠን ወይም ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ 

  8. ይህ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የካላንደር ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡፡ የጨረታው ሳጥን በ21ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ በጎንደር ማተሚያ ድርጅት በአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይፈፀማል፡፡ 

  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪውን ስም አድራሻ የሚመለከት /ህጋዊ ወኪል/ የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 

  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  11. ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልጉ ከድርጅቱ አቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0581-11-16-72 ወይም 09-13-55-44-66 ወይም 058-211-24-46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

  12. የጨረታ ሰነዱን በብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከአዲስ አበባ ግዥ ሰራተኛ ወይም ከዋናው መ/ ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡  

                                                                        የጎንደር ማተሚያ ድርጅት

Save Tender