Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ
  • Address ወልቂጤ ከተማ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251 113658470
  • Website
  • Deadline31 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price150.00
  • Bid Security5,000.00 /አምስት ሺ ብር/
  • opening date2025-10-31 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

የማ/ኢ/ክ/መንግሥት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በጥቅል ግዥ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም

 

የማ/ኢ/ክ/መንግሥት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በጥቅል ግዥ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

  1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕድሳት የፈፀሙ፣ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ከፋይነት /ቲን/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የጨረታ አሸናፈ ከሆኑ ከግዥው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ፣
  4. ከሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ኦንላይን (Online) ሲስተም የምዝገባ /የእቅራቢነት/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት /የሚሞሉት/ የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይንም ያላካተተ መሆን ይኖርበታል።
  6. ከ50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) በላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል ።
  7. ተጫራቾች በዝዙት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፈርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውንና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ቴክኒካል ፋይናንሻል 1 ኦርጂናል እና 1 ኮፒ በማዘጋጀትና ስፔስፍኬሽን ለሚያስፈልጋቸው በተቀመጠው ስፔስፍኬሽን መሰረት በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች ለጨረታው ቀደም ብሎ ለተወደደሩባቸው ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለእያንዳቸው ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያልቀረበባቸው የዕቃ ዓይነቶች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ ።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ራሱን በቻለ ፖስታ አሽገው ለብቻ ወይም በቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ውስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ብር 5,000.00 /አምስት ሺ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  12. የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዘው በመቅረብ የማይመለስ 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) ብቻ በመክፈል 9 ቁጥር ማግኘት ይችላሉ።
  13. ተጫራቾች የዚህን የጨረታ ሰነድ መመሪያ በሚገባ በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 9 ቁጥር ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። በ15ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
  15. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ እና ለወደፊትም በመንግስት ዕቃ/አገልግሎት ግዥ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።
  16. ተጫራቾች ይፋ በሚደረገው ውጤት መሰረት ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነታቸው ተገልፆ ውል በተፈራረሙ በ15 ቀናት ውስጥ ወልቂጤ በሚገኘው የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ መጋዘን ማስረከብ አለባቸው።
  17. ኤጄንሲው በግዥው ዝርዝር ፍላጎት ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
  18. ኤጀንሲው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ 251113658470

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ

ወልቂጤ

 

Save Tender