Tender Detail

Tender Details

  • Company የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት /ሞላሌ/
  • Address በሰ/ሸዋ ዞን የሞላሌ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116220779
  • Website
  • Deadline01 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price50.00
  • Bid Security20%
  • opening date2025-11-01 00:00:00
  • Categories Stationery Materials , Electronics Materials

የጨረታ ቁጥር ጨ/ቁ 001/2018 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ለሚገኙ አገልግሎት ሰጭ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት፡-የፅሕፈት መሣሪያ፡ ሎት2፡-የኤሌከትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች ሎት3፡-የፈርኒቸር እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በማውጣት እቃዎችን ማስቀረብ እና አገልግሎት ላይ ማዋል ይፈልጋል፡፡

የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት /ሞላሌ/


                                                                       ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

                                         የጨረታ ቁጥር ጨ/ቁ 001/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ለሚገኙ አገልግሎት ሰጭ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 

ሎት፡-የፅሕፈት መሣሪያ፡ ሎት2፡-የኤሌከትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች ሎት3፡-የፈርኒቸር እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በማውጣት እቃዎችን ማስቀረብ እና አገልግሎት ላይ ማዋል ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት - 

  1. በዘርፉ የተሰማራና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ 

  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር ያላቸው 

  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ⁄የቫት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡ 

  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 

  5. የሚገዙት እቃዎችን ዓይነትና ብዛት እንዲሁም ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አርቲሜቲክ ቼከ ከተሠራ በኋላ በሚገኘው _ ጠቅላላ ድምር 2% በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንኮች የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት /CPO/ እና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ 

  7. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ከተዘረዘሩትን እቃዎች ውስጥ ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡ 

  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ስልከ ቁጥር ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ 

  9.  በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ 

  10. ማንኛውም ተጫራች የሚገዛውን እቃ ለማቅረብ የገዛውን የጨረታ ሰነድ አንድ ወጥ ማለትም በአንድ ኦርጅናል ፖስታ ብቻ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በእዚሁ እለት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ጨረታው በይፋ ይከፈታል፡፡ 

  11.  ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ላይ ከዋለ የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ ጨረታው የሚከፈተው በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡ 

  12.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መግዣ በማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ 

  13.  ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ወጭ ሞላሌ ከተማ አስተዳደር ንብረት ከፍል ድረስ በማምጣት ጽ/ ቤቱ ባቋቋመው የእቃ ጥራት አረጋጋጭ በማስፈተሽ ንብረቱን ማስረከብ አለባቸው በመሆኑም የሚቀርበ እቃዎች ላይ የጥራት ችግር ቢያጋጥም ተጫራቹ ወይም አቅራቢው ወደዚያው ተመላሽ አድርጎ እቃዎቹን ይተካል፡ 

  14. ሌሎች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተካተቱ /ያልተገለፁ/ ካሉ በግዥ አፈፃፀም መመሪያውና አዋጁ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡ 

  15.  ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ የእያንዳንዱን የእቃ መለኪያ የተሠጠውን የነጠላ ዋጋ ወይም ሌሎች የውል ቃሎች እና ሁኔታዎችን ሳይለወጥ ጨረታው ላይ ያወጣውን እቃ ብዛት ወይም መጠን 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት የተጠበቀ ነው፡፡ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተ በለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-622-07-79 ደውለው ይጠይቁ 

                                                              የሞላሌ ከተማ አስ/ገንዘብ/ፅ/ቤት /ሞላሌ/

Save Tender