የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሠጡ የተለያዩ ከታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሠጡ የተለያዩ ከታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት
- Calcium hypochlorite 45kg /የውሃ ማከሚያ ክሎሪን
- የፓምፕ ጥገና ዕቃዎች
- የቧንቧ ጥርስ ማውጫዎች እና መፍቻዎች
- የእስቴሸነሪና የጽዳት ዕቃዎች
- ከላይ በቁጥር አንድ በተጠቀሰው የዕቃ ዓይነት የሥራ ዘርፍ ላይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ እንዲሁም በዘርፉ በቀጥታ ተሳታፊ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒሰቴር በዚህ ሥራ የተመዘገቡ ስለመሆናቸውን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የተጨማሪ እሴት ታክሰ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ መኖሩን የሚገልጽ ማስረጃ ።
- ተወዳዳሪዎች ሲያሸንፉ ወዲያውኑ ከድርጅቱ ጋር ውል ገብተው በራሱ ትራንስፖርት ወደ ድርጅቱ እስቶር አቅርቦ የጫኝና አውራጅ ችሎ ማስረከብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ቀን የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት ከእያንዳንዱ ዓይነት አንድ ሳምፕል ለውድድር ይዘው መቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ከላይ ለተጠቀሱ የጨረታ ዓይነቶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ cpo ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንት ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ ከድርጅቱ በመውሰድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ/ ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል ለብቻ ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ ለብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል ለብቻ ፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒ ለብቻ አሽጎ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውሰጥ በማስገባት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአርባምንጭ ከተማ ውሃና ፈሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ በ16ኛው ቀን ተጫራቶች /ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል። ሆኖም የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓላት ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል።
- በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 0468810369/0468812049 መደወል ይቻላል።
የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
