Tender Detail

Tender Details

  • Company Federation of Ethiopian Associations of Persons with Disabilities (የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን) (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ)
  • Address ከሰሜን ሆቴል ጀርባ ወደናይጄሪያ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ በር ፊት ለፊት በሚገነጠለው አስፋልት ከ6ዐ - 70 ሜትር ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው መ/ቤታችን : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111553003
  • Websitehttps://www.feapd.org/
  • Deadline31 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security20%
  • opening date2025-10-31 00:00:00
  • Categories Vehicle

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን የተባለ የበጐ አድራጐት ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች አንድ ሚኒባስ መኪናን ጨምሮ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Federation of Ethiopian Associations of Persons with Disabilities (የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን) (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን የተባለ የበጐ አድራጐት ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች አንድ ሚኒባስ መኪናን ጨምሮ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም :-

1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤ.ቁ 1057 የኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ ፊት ለፊት በሚገነጠለው አስፋልት እንቁ ስላሴ ጐዳና 70 ሜትር አካባቢ ገባ ብሎ በሚገኘው ጽ/ቤታችን ከጠዋቱ 3፡00 - 10፡00 ሠዓት ድረስ በአካል ቀርበው ማመልከት ይቻላል፡፡

2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሰርተው ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ፣ በዳሸን ባንከ ወይም በአዋሽ ባንክቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ከ5 የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የሚሸጡትን ንብረቶች መረጃ የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝ እና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ በፌዴሬሽናችን ጽ/ቤት በመቅረብ በአስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡

5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሠነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡

 

6. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘቡን ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዙት ጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጐ ሁለተኛው አሸናፊ ራሱ ባሸነፈበት ዋጋ ከፍሎ እንዲገዛ ይደረጋል፡፡

7. ተጫራቶች የድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ጋር በመቅረብ የንብረቶቹን ሙሉ መረጃ የያዘ ሠነድ በመግዛት ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡

8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከ11ኛ ቀን እስከ 15ኛው ቀን ደግሞ ንብረቶቹ በአካል የሚታዩበት ሲሆን በ15ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

9. ተጫራቶች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

10. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1553003 / 0921324330

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ.)

Save Tender