በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት:የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት
1ኛ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሽ ሲሳይ ያደቴ እና በአፈፃፀም ተከሳሾች ከኛ አስራት ጀንበር 2ኛ. እመቤት ስዩም 3ኛ. ሔለን ከተማ ሶስት ሰዎች መካከል ያለውን የፍርድ አፈፃፀም የፍታብሔር ከርክርአስመልከቶ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምስራቅ ቋሚ ችሎት በቀን 26/01/2018 በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ የፍርድ ባለ ዕዳ ንብረት የሆነ ባለ 2 (ሁለት) ፎቅ ህንፃ እና 1 (አንድ) መሬት (ግራውንድ) (B+G+2) የሆነ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ ከ/ከተማ በዳቱ ወረዳ መስተዳድር ውስጥ 260.30 ካ.ሜ (ሁለት መቶ ስልሳ ነጥብ ሰላሳ ካ.ሜ) መሬት ላይ የሚገኝ የካርታ ቁጥሩ 2323/2001 ሆኖ አቶ ኃይሉ ሰብስቤ በተባለ ሰው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ እና ካርታ በተሰጠበት ወቅት አዋሳኞቹ በምስራቅ ዶ/ር አማኑኤል፣ በምዕራብ የመኖሪያ ቤት፣ በሰሜን መንገድ እና በደቡብ መኖሪያ ቤት የሚያዋስኑት በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር7.534,837 (ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ሰባት) በቀን 08/03/2018 ጠዋት ከ2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ግልፅ በሆነ ጨረታ ይሸጣል፡፡ የጨረታው ውጤት በ10/03/2018 ጠዋት በ4፡00 ሰዓት እንዲቀርብ ታዟል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ላይ ተሳትፋችሁ መግዛት የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
1ኛ. የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25/100 ፐርሰንት ብር 1,883,709.25 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠኝ ብር ከ25/100) በስንቄ ባንክ በሲፒኦ ማስያዝ ወይም 2ኛ. በባንከ የተረጋገጠ ቼከ በማቅረብ መመዝገብ ይቻላል፡፡
3ኛ, ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ ጠዋት ከ2፡30 ሰዓት ጀምሮ ቀርባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት
