በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ ደንብ ልብስ ሎትı (6211)፣አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት2 (6212)፣ህትመት ሎት 3 (6213)፣አላቂ የፅዳት ዕቃዎች ሎት4 (6218)፣ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት5 (6219)፣ለማሽነሪ እና ለፕላንት ጥገና ሎት6 (6243)፣ለፕላንት እና ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ (ቋሚ እቃዎች) ሎት7 (6313)፣አላቂ የህከምና እቃዎች ሎት8 (6214)፣ ለህንፃ እና ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች (የግንባታ እና ፓርቲሽን ስራዎች) ሎት9 (6244)፣ ለመስተንግዶ (ለጤና ተቋሙ ካፍቴሪያ) ሎት10 (6233) የአገልግሎት(የሮቶ እጥበት እና ጥገና) ሎት 11 (6256) ለህንፃ እና ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ሎትı2 (6314) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰቦች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑን ግብር የገበረ ከገቢዎች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና በአቅራቢነት የተመዘገ በማስረጃ ማቅረብ።
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

1. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
2. ማንኛውም ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነት ጠቅላላ ዋጋ እና የአንዱን ዋጋ ከፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በሰጠው ፎርም ላይ መሙላት ይኖርበታል። የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወስዳል።
3. ተጫራቾች ጨረታውን በትከከል በታሸገ እና ሙሉ አድራሻው በትከክል በታወቀ ኤንቨሎፕ በሁለት ፖስታ በማድረግ ከላያቸው ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው መፃፍ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ያቀረቡት CPO ኦርጅናል ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ወይም ዋስትና ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የእቃዎቹን መስፈርቶች አይነት ሳይለወጡና ሳይነካኩ በተሰጠው እስፔሰፊኬሽን መሰረት (ፎርም) ላይበትከከል ሞልተው ማቅረብ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የሚያቀርባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች እስፔስፌኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
6. ለጨረታው የቀረበው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በአጋጣሚ ቢሳሳትና ቢስተካከል በቦታው ፊርማ ሊኖረው ይገባል።
7. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍፁም አይቻልም።
8. ተጫራቾች ጨረታውን በትከከል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000.00 (ሦስት ሺ ብር) ለእያንዳንዳቸው ለሎት1፣2፣3፣4፣5፣6፣7፣10፣11፣12 እና ብር 5000 (አምስት ሺ ብር) ለሎት 8 እና ብር 30000 (ሰላሳ ሺ ብር) ለሎት 9 CPO ማቅረብ ይኖርበታል። ወይም ህጋዊ ዋስትና ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል።
10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡ 30-6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-1፡30 ሰዓት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ መለስተኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቶች ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይሰረዝም።
11. መስሪያቤቱ አሸናፊው ድርጅት እንደታወቀ የጨረታውን ውጤት ወዲያውኑ ያሳውቃል።
12. ማሳሰቢያ፦ ኦርጂናል ፖስታዎች በጨረታ መክፈቻ እና መወዳደሪያ ወቅት የማይከፈት መሆኑን እንገልፃለን። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. አድራሻ:- በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የሚገኝበት ቦታ ቡልጋሪያ አለፍብሎ ከኖክ ማደያ በስተግራ ታጥፎ በሚወሰደው መንገድ 150 ሜትርገባብሎ ከሰኒ ሳይድ ት/ቤት ጀርባ ወይም ከኢንተርናሸናል ከሊኒካል ላብራቶሪ ዝቅ ብሎ ይገኛል።
14. ስልክ ቁጥር 011 4 62 49 47
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ