የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከዚህ በታች በዝርዝር ያስቀመጣቸውን ንብረቶች በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈጸጸም ከሳሽ ወጋገን ባንክ እና በአፈጸጸም ተከሳሽ የቤንች ማጅ አንድነት ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ብር 17,559.496 (አሥራ ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ዘጠና ስድስት) ብር በሆነው የፍርድ ዕዳ ላይ ፍርድ ቤቱ በፍርድ ዕዳ በተከበሩ ንብረቶች ላይ በግልጽ ጨረታ ንብረቶችን አሽጦ ለፍርድ ባለመብት ገንዘቡን ማስከፈል ይረዳ ዘንድ
1ኛ/ ንብረትነቱ የአፈጻጸም ተከሳሽ የሆነው በቤንች ሽኮ ዞን መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ጊቢ ውስጥ ለቢሮ አገልግሎት የሚገለገሉበት ሕንፃ ቢሮ አጠቃላይ ሥፋቱ 450 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈበት በአዋሳኝ በሰሜን የቤንች ሸኮ ዞን መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ በደቡብ የቤንች ሸኮ ዞን መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ አጥር በምሥራቅ ቤንች ሽኮ ዞን ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ በምዕራብ ቤንች ሸኮ ዞን መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ የሚያዋስኑት ንብረትነቱ የሚገኘው በመንግሥት ተቋማት ጊቢ ውስጥ ሲሆን አጠቃላይ ግምቱ 9,303,778.5 (ዘጠኝ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ሥምንት ከአምስት ሳንቲም) ነው፡፡
2ኛ/ ንብረቱ የአፈጻጸም ተከሳሽ የሆነው ሞተር ቁጥር 2GD-8356287 የሻንሲ ቁጥር MRHB8CD3K04757722 የሆነ ቶዮታ አይሉክስ ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ 3,681,776.91 (ሦስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከዘጠና አንድ ሳንቲም) ንብረትነቱ ተከብሮ የሚገኘውም በቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጊቢ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡
3ኛ/ ንብረቱ የአፈጻጸም ተከሳሽ የሆነው ኮድ 3-5024 የሻንሲ ቁጥር MD634KE69F2G41148 የሆነው ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 45,299 (አርባ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር) ሲሆን ንብረትነቱ ተከብሮ የሚገኘው ሥፍራ (ቦታ) በቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጊቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን
- የጨረታው ቦታ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጊቢ ውስጥ በሬጅስትራር አማካይነት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚወጣበት ጊዜ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 1 (አንድ) ወር (30) ቀናት ውስጥ ሆኖ ተጫራቾች በሰም በታሸገ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ዓላማ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ባሉት ቀናት በወሩ መጨረሻው ቀን ከቀኑ 11፡30 የሚዘጋ ሲሆን በነጋታው ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሠዓት ባሉት ጊዜያት (ሠዓታት) ውስጥ ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ገንዘቡን ለፍርድ ባለመበት ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ገንዘቡን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- የፍርድ ባለ ዕዳው ገንዘቡን ለፍርድ ባለመብቱ የጨረታው አሸናፊ ከመታወቁ በፊት ገንዘቡን ለፍርድ ባለመብት የሚከፍል ከሆነ ጨረታው እንደሚሰረዝ ተጫራቾች አውቀው እንዲወዳደሩ ታዟል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
