ሐ/ህ/ክ/መ/ት/ል/ቢሮ የማሽነሪ እና ገልባጭ መኪና ኪራይ አገልግሎትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊ ብቃት ያላቸውን የአገር ውስጥ ተጫራቾች ይጋብዛል።
ሐ/ህ/ክ/መ/ት/መ/ል/ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሐትመልቢ-NCB-06-2018
ሐ/ህ/ክ/መ/ት/ል/ቢሮ የማሽነሪ እና ገልባጭ መኪና ኪራይ አገልግሎትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊ ብቃት ያላቸውን የአገር ውስጥ ተጫራቾች ይጋብዛል። በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ፡-
- የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች ከተጠቀሱት አድራሻዎች የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ዋጋቸውን በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ በወጣ 16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4:30 ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፡-
- በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ለመታደሱ ማረጋገጫ፣
- ማንኛውንም የወቅቱን የመንግሥት ገቢ ግብር ለመክፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋ፣
- በመንግሥት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስከር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ እካል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ የጨረታውን ዋጋ 1% በባንከ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የማሽነሪ እና ገልባጭ መኪና ኪራይ አቅርቦት ቦታ ሐረሪ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ቢሮ ባሎት ሳይቶች መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ የማሽነሪ መጫኛና ማውረጃ ክፍያና ተያያዥ ወጪዎችን በማካተት ማቅረብ አለባቸው።
- ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል።
|
መስሪያ ቤት |
ሐ/ህ/ክ/መ/ት/መ/ል/ቢሮ |
|
ቢሮ ቁጥር |
00 |
|
ፖ.ሳ.ቁጥር |
302 |
|
አድራሻ |
ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ነጩ ህንጻ 3ኛ ወለል |
|
ከተማ |
ሐረር |
|
ሀገር |
ኢትዮጵያ |
ሐ/ህ/ክ/መ/ት/መ/ል/ቢሮ
