በሀድያ ዞን ጎምቦረ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለክላስተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚሰጥ ጽ/መሳሪያን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀድያ ዞን ጎምቦረ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀድያ ዞን ጎምቦረ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለክላስተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚሰጥ ጽ/መሳሪያን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተፋላጊ መስፈርት
1ኛ. በዘርፉ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ የላቸው
2ኛ. የግብር ከፋይነት መለይ ቁጥር ያላቸው
3ኛ. የቫት ከፋይነት ሰርተፍኬት ያላቸው
4ኛ. የአቅረቢነት ፈቃድ ማስረጃ ያላቸው ድርጅቶች በሃድያ ዞን የጎ/ወ/ፋ/ፅ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 100 /አንድ መቶ ብር /ብቻ በመክፈል እንድትገዙና የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በማስያዝ መወዳደር የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታውን መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሃሳብ የያዘውን ፖስታ ኦርጅናል ሰነድ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ቢሮ ቁጥር 01 በሚገኛው የጨረታ ሳጥን እንዲያስገቡና ጨረታውን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
መ/ቤቱ ስለጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኛ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 091618748/092344798 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በማ/ኢ/ክልል/በሃድያ ዞን የጎምቦረ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
