Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011637 58 03
  • Website
  • Deadline27 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-27 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Rent , Construction Machinery , Construction Works

የደብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማነበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባሕርዛፍ ግንድ ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አመር ሀገር አካባቢ እና ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አይሶፌ /መድኃኒዓለም/ አካባቢ ደን ሳይት ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ሥራ ማሠራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን ለ250 ሰዓት በመከራየት ማሠራት ይፈልጋል፡፡

Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማነበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባሕርዛፍ ግንድ ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አመር ሀገር አካባቢ እና ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አይሶፌ /መድኃኒዓለም/ አካባቢ ደን ሳይት ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ሥራ ማሠራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን ለ250 ሰዓት በመከራየት ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ፡-

  1. በዘርፉ የተሰማራና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው እና ስድስት ወር ያላለፈው ጨረታ ለመሣተፍ የሚያበቃ የነቢዎች የጨረታ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
  3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ) CPO/ ማስያዝ አለባቸው
  6. አሸናፊው ድርጅት ማሽኑን በራሱ ወጪ /የሎቤድ ኪራይ ራሱ ችሎ/ ሥራው የሚሠራበት ጫካ ድረስ የማድረስና ሥራውን ሲጨርስ የመመለስ ግዴታ አለበት፤ እንዲሁም የራሱ ኦፕሬተር ሊኖረው ይገባል፡፡ የኦፕሬተር ሰርቪስ ተጫራቹ ማቅረብ አለበት።
  7. የአንዱ ሳይት ሥራ ሲጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ሳይት ማሽኑን የማዘዋወር ኃላፊነት የአከራዩ ድርጅት ኃላፊነት ነው፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራች በሥራ ቦታ ላይ ከነዳጅ ወጪ በስተቀር የኤክስካቫተሩን የዘይት፣ ቅባት፣ ግሪስ፣ ሰርቪስ፣ ቀላልና ከባድ ጥገናዎች፣ የጎማ ጥገናና ግዢ፣ የሹፌር ደመወዝ እና አበል እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በራሳቸው ይሸፍናሉ፡፡
  9. ማሽኑ በሥራ ላይ እያለ ቢበላሽ አሸናፊው ተጫራች በራሱ ወጪ የተበላሸውን የማስተካከል ሥራ የሚሠራ ሲሆን በቀላሉ ማስተካከል የማይችል ከሆነ በራሱ ወጪ አንስቶ በምትኩ ሌላ ማሽን የማስገባት ግዴታ አለበት።
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  11. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
  13. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታግድም፡፡
  14. የመክፈቻ ቀኑ የሕዝብ በዓል ላይ ወይም እሁድ ከዋለ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  15. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል፡፡
  16. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከካምፓኒው ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910368437 ደውለው ይጠይቁ

 

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ደብረ ብርሃን

 

Save Tender