Tender Detail

Tender Details

  • Company Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115571107
  • Websitehttps://awashbank.com/am-et/
  • Deadline20 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ)
  • opening date2025-10-20 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ እና በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ እና በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ/ቁ የተበዳሪው ሙሉ ሥም አበዳሪ      ቅርንጫፍ የንብረት   ማስያዥ ስም የቦታ አገልግሎት ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ የካርታ ቁጥር የቦታ ስፋት በካ.ሜ የጨረታ መነሻ ዋጋ የጨረታ ቀን የጨረታ     ሰዓት
ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ/ወረዳ
1 ጌታሁን መለሰ ጉርድ ሾላ ተበዳሪው ለመኖሪያ ቤት አ.አ ለሚ ኩራ 13 AA000051306240 487 27117377 43162 5:00-6:00
2 ሀጎስ ገብረአናንያ ተክለ ሃይማኖት ተበዳሪው ለመኖሪያ ቤት (ጅምር G+3) አ.አ አቃቂ ቃሊቲ 01 029757 250 6465825 43162 8:00-9:00
3 ማህሌት አፈወርቅ ዋናው መ/ቤት ተበዳሪዋ ለመኖሪያ ቤት አ.አ ቂርቆስ   AA000040401817 475 4100000 43193 5:00-6:00
4 ለሚ ሌሊሳ አንፎ ተበዳሪው ለመኖሪያ ቤት (ኮንዶሚኒየም) ሸገር በኡራዩ   Bur/Kond/192/05 50.09 1327385 43223 5:00-6:00
5 ደረጀ በቀለ አዲሱ ገበያ ወርቁ በቀለ ጅምር G+1 ቤት ጫንጮ   01 CA/2981/2008 810 1750000 43193 5:00-6:00

 

ማሳሰቢያ፡

  1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሰውን ንብረት ጨረታ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳው ወይም ሕጋዊ ወኪሉ፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት የባንኩ ዋናው መ/ቤት ጊዜያዊ ጽ/ቤት በሚገኝበት ህንጻ ውስጥ ይካሄዳል። ከተራ ቁጥር 4-5 የተዘረዘሩት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ንብረቶቹ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል። ተበዳሪው/አስያዡ በጨረታው ቀን ባይገኙም ሃራጁ በተያዘለት ቀን/ጊዜ ይካሄዳል።
  3. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ግን ባንኩ ዋጋውን የሚቀበል መሆን አለመሆኑን ጨረታው ከተደረገበት ቀን ቀጥሎ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለተጫራቹ ያሳውቃል።
  4. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከባንኩ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
  5. ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  6. ከተገነባ ሁለት አመት ከሞላው መኖሪያ ቤቶች ውጭ ባሉ ንብረቶች ሽያጭ ላይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የሚታሰብ ሲሆን ሁሉንም ንብረቶች በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያ ገዢ ይከፍላል።
  7. ለተጨማሪ መረጃ፡- ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ 011-866-80-54፣ ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍ 0112-78-93-76፣ ዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ 0116-18-35-72፣ አንፎ ቅርንጫፍ 011-369-76-28፣ አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ 011-126-81-00፣ ወይም የሕግ አገልግሎት 0115-57-00-75 ብሎ መደወል ወይም በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።
  8. ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አዋሽ ባንክ

Save Tender