Tender Detail

Tender Details


ፍቃዱ ፀጋዬ የንግድ ድርጅት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግንባታ ሥራዎችን በንዑስ ሥራ ተቋራጭ ማሰራት ይፈልጋል።

ፍቃዱ ፀጋዬ የንግድ ድርጅት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ፍቃዱ ፀጋዬ የንግድ ድርጅት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግንባታ ሥራዎችን በንዑስ ሥራ ተቋራጭ ማሰራት ይፈልጋል።

ድርጅታችን በሐረር ከተማ ለሚያስገነባዉ የB+G+10 ሕንፃ ባለ አራት ኮከብ (4) ደረጃ ያለዉ የሆቴል ግንባታ ሥራ

  1. አጠቃላይ የሕንፃዉን የኤሌክትሪክ ዝርጋታ በሥራዉ ዝርዝር መሰረት በደረጃ 3 እና ከዛ በላይ የሆኑ የኤሌክትሪክ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
  2. አጠቃላይ የሕንፃዉን የኮርኒስ ጂፕሰም ቦርድ (Ceiling Gypsum Board) እና የጂፕሰም ቻክ (Gypsum Plastering) ሥራዎች በሥራዉ ዝርዝር መሰረት በአጠቃላይ የሕንፃ ፊንሺንግ (General Building Finishing Work) ሥራ ላይ የተሰማሩ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
  3. አጠቃላይ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችና ለሕንፃዉ የሚያስፈልገዉን የእሳት አደጋ መከላከያ Gp ዝርጋታ ሥራ (Firefighting Gp Installation) እና የኤር ኮንዲሽን (Air Condition with FCU units Installation) ሥራዎች በሥራዉ ዝርዝር መሰረት በኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራ የተሰማሩ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከላይ የተጠቀሱትን ሥራዎች ለመሥራት፡-

  • በሚፈለገዉ ሙያ ላይ ልምድ እና ብቃት ያለው
  • ሶስት (3) እና ከዛ በላይ በተመሳሳይ የሕንፃ አይነት ከላይ የተገለፀዉን ሥራ በጥራት ሰርቶ ያስረከበ
  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለዉና የ2018 ዓ.ም የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።

የሥራው ዝርዝር ያለበትን የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 6 የሥራ ቀናት ቦሌ አዲካ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘዉ ቢሮአችን በሥራ ሰዓት በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ የሚቻል መሆኑን እየገለፅን ጨረታዉም በ7ኛዉ ቀን ተጫራቾችና የጨረታዉ ኮሚቴ በተገኙበት ይከፈታል።

 

Save Tender