የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2018 ዓ.ም በታቀደው መሠረት ለከተማ አስተዳደር ለከተሞች ፎረም አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2018 ዓ.ም በታቀደው መሠረት ለከተማ አስተዳደር ለከተሞች ፎረም አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚገዙ ዕቃዎች - 1) ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
-
በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
-
ተጨማሪ እሴትታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
-
የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር _ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለıo /አስር ቀን/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱ መግዛት ይችላሉ፡፡
-
የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለıo (አስር ቀን) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ⁄ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ጨረታው በከተኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በ4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር :- 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
