Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
  • Address ምስራቅ ጎጃም ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0587760443
  • Website
  • Deadline10 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityለሚወዳደሩበት ጨረታ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2%
  • opening date2025-11-10 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደጀን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በአልማ በጀት የማህበረሰብ አቀፍ መድህኒት ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት


 

የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር-2

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደጀን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በአልማ በጀት የማህበረሰብ አቀፍ መድህኒት ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
  3. በግንባታ ሥራ ደረጃ 7 GC/Bc እና ከዚያ በላይ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ/ የግዥው መጠን /ከ200,000/ ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  6. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር1-5 የተዘረዘሩትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የግንባታ ሰነዱን የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች የተጠየቀውን የትምህርት ቤት ግንባታ ሥራ በጥራት መሥራትና ማስረከብ አለባቸው።
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድረሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ31ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 /አራት/ ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ይከፍታል፡፡
  11. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ዝግ በዓል የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. የጨረታው ተሳታፊዎች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0587760443 መደወል ይቻላል።

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender