የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በከልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ገመኮኤ 01/2018 ዓ/ም
የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በከልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው። .
6. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት ለውሃ ቦቴ በሰዓት ለገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ እና ሎቤድ በኪሜትር ብር10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር100014569768 ገቢ በማድረግ የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ዋናው መ/ቤት ደሴ በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተበሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15/2/2018 ዓ.ም 8.00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ፋይናንስ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ- 16/2 /2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
11. የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል፡
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0331116229 ወይም 0331114423 በመደወል ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
የወሎ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት
